ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላለፍ ወይም በከተማይቱ ኗሪዎች መካከል የሚነሣውን ሕግ ነክ ክርክር በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ ይዳኙ ዘንድ ሌዋውያንን፥ ካህናትንና ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎች አንዳንዶቹን በኢየሩሳሌም ሾመ፤ እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
2 ዜና መዋዕል 17:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም ጋር ዘጠኝ ሌዋውያንና ሁለት ካህናት ነበሩ፤ ሌዋውያኑ ሸማዕያ፥ ነታንያ፥ ዘባድያ፥ ዐሣሄል፥ ሸሚራሞት፥ ይሖናታን፥ ኦዶኒያ፥ ጦቢያና ጦባዶኒያ ሲሆኑ ካህናቱ ደግሞ ኤሊሻማዕና ይሖራም ናቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነዚህም ጋራ ጥቂት ሌዋውያን ነበሩ፤ ስማቸውም፦ ሸማያ፣ ነታንያ፣ ዝባድያ፣ አሣሄል፣ ሰሚራሞት፣ ዮናታን፣ አዶንያስ፣ ጦብያና ጦባዶንያ ነበር። ካህናቱ ደግሞ ኤሊሳማና ኢዮራም ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዝባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናትንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያን፥ ጦባዶንያን ላከ ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን አብሮ ላከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዛባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናታንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያን፥ ጦባዶንያስን ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን፥ ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዝባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናትንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያንና ጦባዶንያን ሰደደ፤ ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን ሰደደ። |
ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላለፍ ወይም በከተማይቱ ኗሪዎች መካከል የሚነሣውን ሕግ ነክ ክርክር በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ ይዳኙ ዘንድ ሌዋውያንን፥ ካህናትንና ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎች አንዳንዶቹን በኢየሩሳሌም ሾመ፤ እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
እንዲሁም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለለዩ፥ የመላው እስራኤል መምህራን ለሆኑ ሌዋውያን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦ “የተቀደሰውን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ልጅ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑሩት፤ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ማገልገል እንጂ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት በትከሻችሁ ተሸክማችሁ ከስፍራ ወደ ስፍራ መውሰድ የለባችሁም።