1 ጢሞቴዎስ 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሴቶች በመጀመሪያ ለክርስቶስ የገቡትን ቃል በማፍረሳቸውም በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ፍርድን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ፤ በመጀመሪያ የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም በመጀመሪያ የገቡትን ቃል በማፍረሳቸው ምክንያት በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤ |
መሰብሰባችሁ ለፍርድ እንዳይሆን ከመካከላችሁ የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር እኔ እዚያ ስመጣ ተጨማሪ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።
ባሎቻቸው የሞቱባቸው በዕድሜ ያልገፉ ሴቶች ሥጋዊ ምኞታቸው አሸንፎአቸው ለክርስቶስ ያላቸው ፍቅር ሲቀነስ ባል ማግባት ስለሚፈልጉ እነርሱን በመበለቶች መዝገብ አትጻፋቸው።
ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ።
ፍርድ የሚጀመርበት ጊዜ ቀርቦአል፤ ፍርዱ የሚጀመረውም በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ነው፤ ታዲያ፥ ፍርድ የሚጀመረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?