1 ሳሙኤል 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዩም “እነሆ እኔ የአንድ ጥሬ ብር አንድ አራተኛው እጅ አለችኝ፤ እርስዋን እሰጠዋለሁ፤ እርሱም አህዮቹን የት ማግኘት እንደምንችል ይነግረናል” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዩ፣ “እኔ የአንድ ሰቅል ጥሬ ብር ሩብ አለኝ፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረን ዘንድ ገንዘቡን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ” ሲል በድጋሚ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዩ፦ “እነሆ፥ እኔ የአንድ ጥሬ ብር አንድ አራተኛው እጅ አለኝ፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ” ሲል በድጋሚ ለሳኦል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናው ደግሞ ለሳኦል መልሶ፥ “እነሆ፥ በእጄ የብር ሰቅል ሩብ አለኝ፤ እርሱንም ለእግዚአብሔር ሰው ትሰጠዋለህ፤ የምንሄድበትን መንገድም ይነግረናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናው ደግሞ ለሳኦል መልሶ፦ እነሆ፥ በእጄ የሰቅል ብር ሩቡ አለኝ፥ እርሱንም መንገዳችንን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጣለሁ አለ። |
አገልጋዩም “ቈይ! እስቲ በዚህች ከተማ በጣም የተከበረ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ፤ እርሱ የሚናገረው ቃል ሁሉ በትክክል ይፈጸማል፤ ስለዚህም ወደ እርሱ እንሂድ፤ ምናልባትም አህዮቹን የት ማግኘት እንደምንችል እርሱ ሊነግረን ይችል ይሆናል” ሲል መለሰለት።