በአቤሴሎም ጋባዥነት ከእርሱ ጋር ከኢየሩሳሌም የሄዱ ሁለት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ተከትለውት የሄዱት ስለ ሤራው ምንም ነገር ሳያውቁ በቅንነት ነበር።
1 ሳሙኤል 9:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ከተማው እንደ ገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ፤ መሥዋዕቱን መባረክ ስላለበት ሕዝቡ እርሱ ከመምጣቱ በፊት አይበሉም፤ ከዚያም በኋላ ተጋባዦቹ ይበላሉ፤ ፈጥናችሁ ውጡ፤ አሁን ታገኙታላችሁ” አሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ከተማዪቱም በገባችሁ ጊዜ፣ ለመብላት ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን እርሱ መባረክ ስላለበት፣ እርሱ እስኪመጣ ድረስ ሕዝቡ መብላት አይጀምርም፤ ከዚያ በኋላ የተጋበዘው ሕዝብ ይበላል፤ አሁኑኑ ውጡ፤ ወዲያው ታገኙታላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ከተማዪቱም በገባችሁ ጊዜ፥ ለመብላት ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን እርሱ መባረክ ስላለበት ሕዝቡ እርሱ ከመምጣቱ በፊት አይበላም፤ ከዚያ በኋላ የተጋበዘው ሕዝብ ይበላል፤ አሁኑኑ ውጡ፤ ወዲያው ታገኙታላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ከተማዪቱም በገባችሁ ጊዜ ለመብላት ወደ ባማ ኮረብታ ሳይወጣ በከተማው ውስጥ ታገኙታላችሁ፤ መሥዋዕታቸውን እርሱ የሚባርክ ስለሆነ እርሱ ሳይወጣ ሕዝቡ ምንም አይቀምሱምና፥ ከዚያም በኋላ እንግዶች ይበላሉና፤ በዚህም ጊዜ ታገኙታላችሁና አሁን ውጡ” አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ከተማይቱም በገባችሁ ጊዜ መሥዋዕቱን እርሱ የሚባርክ ስለ ሆነ እርሱ ሳይወጣ ሕዝቡ ምንም አይቀምሱምና፥ ከዚያም በኋላ የተጠሩት ይበላሉና ለመብላት ወደ ኮረብታው መስገጃ ሳይወጣ ታገኙታላችሁ፥ በዚህም ጊዜ ታገኙታላችሁና አሁን ውጡ አሉአቸው። |
በአቤሴሎም ጋባዥነት ከእርሱ ጋር ከኢየሩሳሌም የሄዱ ሁለት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ተከትለውት የሄዱት ስለ ሤራው ምንም ነገር ሳያውቁ በቅንነት ነበር።
ከዚህ በኋላ ሕዝቡ በመስኩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ አንሥቶ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና የምስጋና ጸሎት አደረገ፤ እንጀራውንም ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ዐደሉ።
ኢየሱስም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ አንሥቶ፥ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፤ እንጀራውንም ቈርሶ ለሰዎቹ እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ እንዲሁም ሁለቱን ዓሣ ለሁሉም አከፋፈለ።
ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ቈርሶም ለሰዎቹ እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንጀራውን አንሥቶ ምስጋና ካቀረበ በኋላ ለተቀመጡት ሰዎች ዐደላቸው። እንዲሁም ዓሣዎቹን አከፋፈላቸው፤ ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን ያኽል አገኙ።
ለእኔም እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤ የሚያደርግ አንድ ታማኝ ካህን አስነሣለሁ፤ ለእርሱም የጸና ዘር እመሠርትለታለሁ፤ እኔ በቀባሁትም ንጉሥ ፊት ይመላለሳል።
ከዚያም በኋላ ሳኦልና አገልጋዩ ወደ ከተማይቱ ወጡ፤ ወደ ከተማይቱም በመግባት ላይ ሳሉ ሳሙኤል ወደ ማምለኪያው ስፍራ ለማለፍ ወደ እነርሱ አቅጣጫ ሲመጣ አዩት።