1 ሳሙኤል 8:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም እነርሱ ያሉትን ሁሉ አዳመጠ፤ ከዚያም ሄዶ ለእግዚአብሔር ነገረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ሕዝቡ ያለውን ሁሉ ሰማ፤ ያንኑ በእግዚአብሔር ፊት ተናገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ሕዝቡ ያለውን ሁሉ ሰማ፤ ያንኑ ለጌታ ተናገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም የሕዝቡን ቃል ሁሉ ሰማ፤ ለእግዚአብሔርም ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም የሕዝቡን ቃል ሁሉ ሰማ፥ ለእግዚአብሔርም ተናገረ። |
ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ መሪዎች ጋር ሄደ። ሕዝቡም ገዢአቸውና መሪያቸው አደረጉት፤ ዮፍታሔም በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ጉዳይ መስማማቱን ገለጠ።