“አባትህ ሰሎሞን በእኛ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖ አስጨንቆን ነበር፤ አሁን ይህን ከባድ ሸክም ብታቃልልልንና ኑሮአችንን ብታሻሽልልን እኛ ለአንተ እንገዛልሃለን” አሉት።
1 ሳሙኤል 8:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከበግና ከፍየል መንጋዎቻችሁ ከዐሥር አንዱን ይወስዳል፤ እናንተም የእርሱ ባሪያዎች ትሆናላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከበግና ከፍየል መንጎቻችሁ አንድ ዐሥረኛውን ለራሱ ይወስዳል፤ እናንተ ራሳችሁም ባሪያዎቹ ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከበግና ከፍየል መንጎቻችሁ አንድ ዐሥረኛውን ለራሱ ይወስዳል፤ እናንተም ባርያዎቹ ትሆናላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከላሞቻችሁ፥ ከበጎቻችሁና ከፍየሎችቻችሁም ዐሥራት ይወስዳል፤ እናንተም ባሪያዎች ትሆኑታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከበጎቻችሁና ከፍየሎቻችሁ አሥራት ይወስዳል፥ እናንተም ባሪያዎች ትሆኑታላችሁ። |
“አባትህ ሰሎሞን በእኛ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖ አስጨንቆን ነበር፤ አሁን ይህን ከባድ ሸክም ብታቃልልልንና ኑሮአችንን ብታሻሽልልን እኛ ለአንተ እንገዛልሃለን” አሉት።
አብርሃምም ከያዘው ነገር ሁሉ ዐሥራት አውጥቶ ሰጠው፤ የመልከ ጼዴቅ የስሙ ትርጓሜ አንደኛው “የጽድቅ ንጉሥ” ሌላው “የሳሌም ንጉሥ” ወይም “የሰላም ንጉሥ” ማለት ነው።
ጎልያድ ተነሥቶ በመቆም በእስራኤል ሠራዊት ላይ እንዲህ እያለ ይደነፋባቸው ጀመር፦ “አሁን በዚያ ቦታ ለጦርነት የተሰለፋችሁት ከቶ ምን ልታደርጉ ነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ ነኝ፤ እናንተ ደግሞ የሳኦል ባሪያዎች ናችሁ፤ እንግዲህ ከእኔ ጋር የሚዋጋ አንድ ሰው ከወታደሮቻችሁ መካከል ምረጡና ወደ እኔ መጥቶ ይግጠመኝ።
ያ ዘመን በደረሰ ጊዜ የመረጣችሁት ንጉሥ ስለሚፈጽምባችሁ በደል በመረረ ሁኔታ ማጒረምረም ትጀምራላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን አቤቱታችሁን አያዳምጥም።”