ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤
1 ሳሙኤል 7:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በምጽጳ መሰብሰባቸውንም ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች አደጋ ሊጥሉባቸው ወጡ፤ እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል በምጽጳ መሰብሰባቸውን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ የፍልስጥኤማውያን ገዦች ሊወጓቸው ወጡ፤ እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ፣ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያንም እስራኤል በምጽጳ መሰብሰባቸውን በሰሙ ጊዜ፥ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ሊወጓቸው ወጡ። እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም የእስራኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ተሰበሰቡ በሰሙ ጊዜ የፍልስጥኤማውያን አለቆች በእስራኤል ላይ ዘመቱ፤ የእስራኤልም ልጆች ሰምተው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም የእስራኤል ልጆች ወደ ምጽጳ እንደ ተሰበሰቡ በሰሙ ጊዜ የፍልስጥኤማውያን አለቆች በእስራኤል ላይ ወጡ፥ የእስራኤልም ልጆች ሰምተው ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ። |
ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤
እስራኤላውያን ሁኔታው አስጊ መሆኑን ባዩና ሠራዊቱም መዋከቡን በተመለከቱ ጊዜ በዋሻ፥ በሾኽ ቊጥቋጦ፥ በአለቶች መካከል በጒድጓዶችና በጒድባ ውስጥ ተሸሸጉ፤