እግዚአብሔርም በእስራኤል ሠራዊት ፊት አሞራውያን በድንጋጤ እንዲሸበሩ አደረገ፤ እስራኤላውያንም እነርሱን በገባዖን ዐረዱአቸው፤ የቀሩትንም በቤትሖሮን በኩል እስከ ተራራው መተላለፊያ ቊልቊለት እስከ ዐዜቃና እስከ ማቄዳ ድረስ አሳደዱአቸው።
1 ሳሙኤል 7:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም ከምጽጳ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን እስከ ቤትካር በታች እያሳደዱ በየመንገዱ ገደሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም ከምጽጳ ወጥተው ፍልስጥኤማውያንን በየመንገዱ እየገደሉ ከቤትካር በታች እስካለው ስፍራ ድረስ አሳደዷቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያንም ከምጽጳ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን እስከ ቤትካር በታች እያሳደዱ በየመንገዱ ገደሉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሰዎች ከመሴፋ ወጡ፤ ፍልስጥኤማውያንንም አሳደዱ፤ በቤኮር ታችም እስኪደርሱ ድረስ መቱአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ከምጽጳ ወጡ፥ ፍልስጥኤማውያንንም አሳደዱ፥ በቤትካር ታችም እስኪደርሱ ድረስ መቱአቸው። |
እግዚአብሔርም በእስራኤል ሠራዊት ፊት አሞራውያን በድንጋጤ እንዲሸበሩ አደረገ፤ እስራኤላውያንም እነርሱን በገባዖን ዐረዱአቸው፤ የቀሩትንም በቤትሖሮን በኩል እስከ ተራራው መተላለፊያ ቊልቊለት እስከ ዐዜቃና እስከ ማቄዳ ድረስ አሳደዱአቸው።
ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በማቅረብ ላይ ሳለ ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ለመውጋት ዘመቱ፤ ነገር ግን በዚያች ቀን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ከፍተኛ ነጐድጓድ አንጐድጒዶ አርበደበዳቸው፤ እነርሱም ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ።