ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል።
1 ሳሙኤል 6:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ታቦትና ከእርሱ ጋር የነበረውን ወርቅ የሞላበት ሣጥን አንሥተው በታላቁ ቋጥኝ ላይ አስቀመጡ፤ የቤትሼሜሽም ሰዎች የሚቃጠልና ሌላውንም መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋውያኑም የእግዚአብሔርን ታቦት፣ የወርቅ ዕቃዎቹን ከያዘው ሣጥን ጋራ አውርደው በትልቁ ድንጋይ ላይ አኖሩ። በዚያችም ዕለት የቤትሳሚስ ሕዝብ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ መሥዋዕቶችንም ሠዉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌዋውያኑም የጌታን ታቦትና የወርቅ ዕቃዎቹን የያዘውን ሣጥን አውርደው በትልቁ ቋጥኝ ላይ አኖሩ። በዚያችም ዕለት የቤትሼሜሽ ሕዝብ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ መሥዋዕቶችንም ሠዉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት፥ ከእርስዋም ጋር የነበረውን የወርቅ ዕቃ ያለበትን ሣጥን አወረዱ፤ በታላቁም ድንጋይ ላይ አኖሩት፤ በዚያም ቀን የቤትሳሚስ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቍርባን አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት፥ ከእርሱ ጋር የነበረውንም የወርቅ ዕቃ ያለበትን ሣጥን አወረዱ፥ በታላቁም ድንጋይ ላይ አኖሩት፥ በዚያም ቀን የቤትሳሚስ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ መሥዋዕትንም ሠዉ። |
ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል።
የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጡ፦ “የሌዊ ዘር የሆኑት ካህናት የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ሲነሡ በምታዩበት ጊዜ፥ ሰፈሩን ለቃችሁ እነርሱን ተከተሉ።
እንዲሁም ከተላኩት መካከል በተመሸጉ ከተሞችና ቅጽር ባልተሠራላቸው መንደሮች ሆነው አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሩት በእያንዳንዱ ከተማ ስም በአይጥ አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች ነበሩ። በቤትሼሜሽ በሚኖረው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታቦት ያኖሩበትም ታላቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ድረስ ምስክር ሆኖ ይታያል።