ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል።
1 ሳሙኤል 6:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤትሼሜሽም ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው በተመለከቱም ጊዜ ታቦቱን አዩ፤ ያንንም በማየታቸው እጅግ ደስ አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የቤትሳሚስ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው ሲመለከቱም ታቦቱን በማየታቸው በጣም ደስ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የቤትሼሜሽ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው ሲመለከቱም ታቦቱን በማየታቸው በጣም ደስ አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቤትሳሚስ ሰዎችም በእርሻ ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ዐይናቸውንም ከፍ አድርገው የእግዚአብሔርን ታቦት አዩ፤ ደስ ብሎአቸውም ተቀበሉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቤትሳሚስ ሰዎችም በሸለቆው ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፥ ዓይናቸውንም ከፍ አድርገው ታቦቱን አዩ፥ በማየታቸውም ደስ አላቸው። |
ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል።
ላሞቹም መንገዱን ሳይለቁና ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳያዘነብሉ በቀጥታ ወደ ቤትሼሜሽ በማምራት ጒዞአቸውን ቀጠሉ፤ በሚሄዱበትም ጊዜ እምቧ ይሉ ነበር፤ አምስቱ የፍልስጤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ድረስ በመከተል ሸኙአቸው።
ሠረገላውም በቤትሼሜሽ ወደሚኖር ኢያሱ ተብሎ ወደሚጠራው ሰው እርሻ መጥቶ በትልቅ ቋጥኝ አጠገብ ሲደርስ ቆመ። ሕዝቡም የሠረገላውን እንጨት ፈለጡ፤ ላሞቹንም ዐርደው ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡአቸው።