1 ሳሙኤል 6:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በፍልስጥኤም ሰባት ወር ከቈየ በኋላ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን ግዛት ሰባት ወር ቈየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም ታቦት በፍልስጥኤማውያን ሀገር ሰባት ወር ተቀመጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ታቦት በፍልስጥኤማውያን ሀገር ሰባት ወር ተቀመጠች። ምድራቸውም አይጦችን አወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን አገር ሰባት ወር ተቀመጠ። |
በማግስቱም ማለዳ የአሽዶድ ሰዎች ተነሥተው ሲመለከቱ የዳጎን ምስል ሐውልት በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ አዩት፤ ከዚያም አንሥተው ቀድሞ በነበረበት ስፍራ አቆሙት፤
ሕዝቡ ካህናታቸውንና አስማተኞቻቸውን ጠርተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁአቸው፤ “ስለ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ምን ማድረግ የሚሻለን ይመስላችኋል? ወደ ስፍራው እንዲመለስ ብናደርግ በምን ሁኔታ እንላከው? ዘዴውን ንገሩን” አሉአቸው።