በዚህ ጊዜ የጸሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን እንዴት ይራገማል? እኔ ሄጄ ራሱን ልቊረጠው!” አለው።
1 ሳሙኤል 24:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ማንን ለመግደል እንደሚጥር ተመልከት! ማንንም እንደሚያሳድድ አስተውል! የሞተ ውሻን ወይስ ቁንጫን? ማንን እንደሚያሳድድ ተመልከት! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤል ንጉሥ የወጣው በማን ላይ ነው? አንተስ የምታሳድደው ማንን ነው? የሞተ ውሻን? ወይስ ቍንጫ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥንት፥ ‘ክፋት ክፋትን ይወልዳል’ እንደተባለ፤ አሁንም እጄ በአንተ ላይ አትሆንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጥንት ምሳሌ፦ ‘ከኀጢአተኞች ኀጢአት ይወጣል’ እንደሚል፥ እጄ ግን በአንተ ላይ አትሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ንጉሥ ማንም ለማሳደድ መጥቶአል? አንተስ ማንን ታሳድዳለህ? የሞተ ውሻን ወይስ ቁንጫን ታሳድዳለህን? |
በዚህ ጊዜ የጸሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን እንዴት ይራገማል? እኔ ሄጄ ራሱን ልቊረጠው!” አለው።
የኢያቡስቴ ቃል አበኔርን በጣም አስቈጣው፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ ወደ ይሁዳ ነገድ የዞርኩ የማልጠቅም ውሻ ነኝን? እኔ ለአባትህ ቤት፥ ለወንድሞቹና ለወዳጆቹ ታማኝነትን አሳይቼአለሁ፤ አንተንም ለዳዊት አሳልፌ አልሰጠሁህም፤ ታዲያ፥ አንተ ስለዚህች ሴት ትወቅሰኛለህን?
ከዚያም በኋላ ዳዊት ቤተሰቡን ሰላም ለማለት ወደ ቤት ገባ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጣችና “የእስራኤል ንጉሥ ዛሬ ትልቅ ስም አግኝቶአል! በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ ቅሌታም ሽማግሌ እርቃኑን ገልጦአል!” አለችው።
ኤልዛቤልም “እንግዲህ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ሆነህ ሳለህ እንደዚህ መሆን ይገባሃልን? ይልቅስ ተነሥ፤ በመደሰትም እህል ውሃ ቅመስ፤ እኔ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ እንድታገኝ አደርጋለሁ!” አለችው።
ከእግዚአብሔር ርቄ በባዕድ አገር እንድገደል አታድርግ፤ ይህን ያኽል ታላቅ የሆነ የእስራኤል ንጉሥ እንደ ቁንጫ የምቈጠረውን እኔን ስለምን ያሳድዳል? እንደ በረሓ ቆቅ የሚያድነኝስ ስለምንድን ነው?”