1 ሳሙኤል 23:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሳኦልም ዳዊት ወደ ቀዒላ መምጣቱ በተነገረው ጊዜ “እግዚአብሔር እርሱን በእጄ ሊጥልልኝ ነው፤ ዳዊት የግንብ ቅጽርና የተመሸጉ የቅጽር በሮች ወዳሉአት ከተማ በመዝለቁ ራሱን በወጥመድ ውስጥ አስገብቶአል” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል የዳዊትን ወደ ቅዒላ መሄድ በሰማ ጊዜ፣ “ዳዊት መዝጊያና የብረት መወርወሪያ ወዳላት ከተማ መግባቱ፣ ራሱን በራሱ እንደ ማሰር ስለ ሆነ፣ ይህን ሰው እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል የዳዊትን ወደ ቅዒላ መሄድ በሰማ ጊዜ፥ “ዳዊት መዝጊያና የብረት መወርወሪያ ወዳላት ከተማ መግባቱ፥ ራሱን በራሱ እንደ ማሰር ስለ ሆነ፥ ይህን ሰው እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ቢሰጠኝ ነው” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሳኦልም ዳዊት ወደ ቂአላ እንደ መጣ ተነገረው፤ ሳኦልም፥ “መዝጊያና መወርወሪያ ወዳለባት ከተማ ገብቶ ተገኝቶአልና እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶታል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዳዊት ወደ ቅዒላ እንደ መጣ ሰማ፥ ሳኦልም፦ መዝጊያና መወርወሪያ ወዳለባት ከተማ ገብቶ ተገኝቶአልና እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶታል አለ። |
ዳዊት በዚፍ አጠገብ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በኮረብታማው አገር ተሸሽጎ ኖረ፤ ሳኦልም እርሱን ለማግኘት ዘወትር ይፈልገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዳዊትን ለሳኦል አሳልፎ አልሰጠውም፤