እግዚአብሔርም ‘እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ?’ አለው። መንፈሱም ‘ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ’ ሲል መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ‘እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል አለው።’ ”
1 ሳሙኤል 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ከእግዚአብሔር የተላከ ክፉ መንፈስ ሳኦልን ተቈራኘው፤ እርሱም ጦሩን በእጁ እንደ ያዘ በቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ ዳዊትም በዚያው በገናውን ይደረድር ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሳኦል ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ መጣበት፤ ዳዊት በገናውን ይደረድር ነበር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሳኦል ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦ ሳለ፥ ከጌታ ዘንድ ክፉ መንፈስ መጣበት፤ ያንጊዜ ዳዊት በገናውን ይደረድር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦ ሳለ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው። ዳዊትም በእጁ በገና ይመታ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦ ሳለ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው። ዳዊትም በእጁ በገና ይመታ ነበር። |
እግዚአብሔርም ‘እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ?’ አለው። መንፈሱም ‘ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ’ ሲል መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ‘እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል አለው።’ ”
ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! በገና መደርደር የሚያውቅ ሰው ፈልገን እንድናመጣልህ እዘዘን፤ ከዚያም በኋላ ክፉ መንፈስ በሚመጣብህ ጊዜ ያ ሰው በገና ይደረድርልሃል፤ አንተም እንደገና ጤናማ ትሆናለህ።”
ከፍልስጥኤማውያን ጋር ይደረግ የነበረውም ጦርነት እንደገና አገረሸ፤ ሆኖም ዳዊት በእነርሱ ላይ ብርቱ አደጋ በመጣል ድል ስለ መታቸው ሸሽተው ሄዱ፤
ከዕለታት አንድ ቀን ሳኦል ጦሩን በእጁ እንደ ያዘ በጊብዓ በሚገኝ ኮረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ በሚጠራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ነበር፤ ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ በዚህን ጊዜ ዳዊትና ተከታዮቹ በአንድ ስፍራ መኖራቸው ለሳኦል ተነገረው፤