ዳዊትም “መልካም ነው! ከአንተ ጋር ስምምነት አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንተ በቅድሚያ የምትፈጽምልኝ ነገር አለ፤ ይኸውም ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ይዘህ ካልመጣህ መገናኘት አንችልም” አለው።
1 ሳሙኤል 18:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ሜልኮል ተብላ የምትጠራው የሳኦል ልጅ ዳዊትን ወደደች፤ ሳኦልም ይህን በሰማ ጊዜ ደስ አለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደችው፤ ሳኦልም ይህን ሲሰማ ደስ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደችው፤ ሳኦልም ይህን ሲሰማ ደስ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደች፤ ይህም ወሬ ለሳኦል ደረሰለት፤ ነገሩም ደስ አሰኘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደች፥ ይህም ወሬ ለሳኦል ደረሰለት፥ ነገሩም ደስ አሰኘው። |
ዳዊትም “መልካም ነው! ከአንተ ጋር ስምምነት አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንተ በቅድሚያ የምትፈጽምልኝ ነገር አለ፤ ይኸውም ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ይዘህ ካልመጣህ መገናኘት አንችልም” አለው።
ታቦቱን ይዘው ወደ ከተማ በሚገቡበት ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ተመለከተች፤ ንጉሡ ዳዊት እየዘለለ ሲያሸበሽብ አይታም በልብዋ ናቀችው፤
ከዚያም በኋላ ዳዊት ቤተሰቡን ሰላም ለማለት ወደ ቤት ገባ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጣችና “የእስራኤል ንጉሥ ዛሬ ትልቅ ስም አግኝቶአል! በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ ቅሌታም ሽማግሌ እርቃኑን ገልጦአል!” አለችው።