1 ሳሙኤል 18:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም የዳዊትን ተልእኮ መሳካት እየተመለከተ በይበልጥ ይፈራው ጀመር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ ዳዊት እንደ ተሳካለት ባየ ጊዜ ፈራው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ ዳዊት እንደ ተሳካለት ባየ ጊዜ ከመቼውም ጊዜ በላይ ፈራው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም እጅግ ብልህ እንደ ሆነ አይቶ እጅግ ፈራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም እጅግ ብልህ እንደ ሆነ አይቶ እጅግ ፈራው። |
ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።
ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሚገኘው ጥበብ በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ ታዛዥ፥ ምሕረት አድራጊ፥ ጥሩ ፍሬ የሞላበት፥ አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።