1 ሳሙኤል 16:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ሳኦል ወደ እሴይ መልእክት ልኮ “ዳዊትን ወድጄዋለሁ፤ ስለዚህ እዚህ በመቈየት ያገልግለኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሳኦል፣ “ዳዊትን ወድጄዋለሁና ከእኔ ዘንድ ሆኖ እንዲያገለግለኝ ፍቀድልኝ” ብሎ ወደ እሴይ ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሳኦል፥ “ዳዊትን ወድጄዋለሁና ከእኔ ዘንድ ሆኖ እንዲያገለግለኝ ፍቀድልኝ” ብሎ ወደ እሴይ ላከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ወደ እሴይ፥ “በዐይኔ ሞገስ አግኝቶአልና ዳዊት በፊቴ እባክህ ይቁም፥” ብሎ ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ወደ እሴይ፦ በዓይኔ ሞገስ አግኝቶአልና ዳዊት በፊቴ፥ እባክህ፥ ይቁም ብሎ ላከ። |
እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤ ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም።
ምግባቸውና የሚጠጡት የወይን ጠጅ ከንጉሡ ማእድ እንዲሆን ታዘዘላቸው፤ በዚህ ዐይነት ለሦስት ዓመት ከሠለጠኑ በኋላ በንጉሡ ፊት ቀርበው የቤተ መንግሥት ሥራቸውን እንዲጀምሩ ተወሰነ።
ነገር ግን የአንተ ረዳት የሆነው የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደ ምድሪቱ ይገባል፤ ምድሪቱን ይወርሱ ዘንድ እስራኤልን የሚመራ እርሱ ስለ ሆነ አበረታታው።’
ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር የተላከ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ዳዊት በገናውን አንሥቶ ይደረድራል፤ ክፉውም መንፈስ ለቆት ስለሚሄድ ሳኦል እየተሻለው እንደገና ጤናማ ይሆናል።