1 ሳሙኤል 15:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም “በእርግጥ በደል ሠርቼአለሁ፤ ይሁን እንጂ ሌላው ቢቀር በሕዝቤ መሪዎችና በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር አብረህ ሂድ” ሲል ለመነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም መልሶ፣ “ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ ነገር ግን በሕዝቤ አለቆች ፊትና በእስራኤል ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ እባክህ ዐብረኸኝ ተመለስ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም መልሶ፥ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ነገር ግን በሕዝቤ አለቆች ፊትና በእስራኤል ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለጌታ እሰግድ ዘንድ እባክህ አብረኸኝ ተመለስ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “በድያለሁ፤ አሁንም በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት እባክህ አክብረኝ፤ ለአምላክህም ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ በድያለሁ፥ አሁን ግን በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት፥ እባክህ፥ አክብረኝ፥ ለአምላክህም ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተምለስ አለው። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
ሳኦልም “በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመልሰህ ወደ እኔ ና፤ ዳግመኛ ልጐዳህ ከቶ አልፈልግም፤ በዛሬይቱ ሌሊት ሕይወቴን አትርፈሃል፤ እኔ እንደ ሞኝ ሆኜአለሁ! ከባድ የሆነ ስሕተትም ፈጽሜአለሁ!” ሲል መለሰ።