ነገር ግን ነቢዩ አኪያ ወደ በሩ ስትቀርብ የኮቴዋን ድምፅ ሰምቶ እንዲህ አላት፥ “ግቢ! የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤ ሌላ ሴት ለመምሰል ስለምን ሞከርሽ? ለአንቺ እነግርሽ ዘንድ የታዘዝኩት አሳዛኝ ዜና አለ።
1 ሳሙኤል 15:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም “ተወው በቃ፤ እግዚአብሔር ትናንትና ማታ የገለጠልኝን እነግርሃለሁ” አለው። ሳኦልም “እሺ ንገረኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “ስማ! ትናንት ማታ እግዚአብሔር የነገረኝን ልንገርህ?” አለው። ሳኦልም፣ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ስማ! ትናንት ማታ ጌታ የነገረኝን ልንገርህ?” አለው። ሳኦልም፥ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ስማ፤ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ” አለው፤ እርሱም፥ “ተናገር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሳኦልን፦ ቆይ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ አለው፥ እርሱም፦ ተናገር አለው። |
ነገር ግን ነቢዩ አኪያ ወደ በሩ ስትቀርብ የኮቴዋን ድምፅ ሰምቶ እንዲህ አላት፥ “ግቢ! የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤ ሌላ ሴት ለመምሰል ስለምን ሞከርሽ? ለአንቺ እነግርሽ ዘንድ የታዘዝኩት አሳዛኝ ዜና አለ።
እንግዲህ ተነሥታችሁ ባላችሁበት ቁሙ፤ የቀድሞ አባቶቻችሁንና እናንተን ለማዳን እግዚአብሔር ያደረገላችሁን ድንቅ ሥራዎች ሁሉ በማስታወስ እነሆ እኔ በእግዚአብሔር ፊት እፋረዳችኋለሁ፤
ሳኦልም “እነርሱ ወታደሮቼ ከዐማሌቃውያን የማረኩአቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጥ የሆኑትን የቀንድ ከብቶችና በጎች ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ አምጥተዋል፤ የቀሩትን ግን በሙሉ ደምስሰናል” ሲል መለሰለት።
ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንተ ስለ ራስህ የነበረህ ግምት አነስተኛ ቢሆንም የእስራኤል ነገዶች መሪ አልሆንክምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል፤
ወደ ከተማይቱም ዳርቻ በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን “አገልጋይህ ቀድሞን ወደ ፊት እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ አገልጋዩም ቀድሞ ከሄደ በኋላ ሳሙኤል ሳኦልን እንደገና “አንተ እዚህ ትንሽ ቈይ፤ እኔም እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው።