እነርሱም የሚሉትን ትሰማለህ፤ ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤”። ስለዚህ ጌዴዎንና አገልጋዩ ፑራ ወደ ጠላት ሰፈር ዳርቻ ወረዱ፤
1 ሳሙኤል 14:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ‘ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ በዚያ ጠብቁን’ ቢሉን፥ ባለንበት እንቈያለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ ‘ወደ እናንተ እስክንመጣ እዚያው ጠብቁን’ ካሉን፣ ባለንበት ሆነን እንጠብቃቸዋለን፤ ወደ እነርሱም አንወጣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ ‘ወደ እናንተ እስክንመጣ እዚያው ጠብቁን’ ካሉን፥ ስፍራችንን ይዘን እንጠብቃቸዋለን፤ ወደ እነርሱም አንወጣም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፦ እስክንነግራችሁ ድረስ ርቃችሁ ቈዩ ቢሉን ርቀን እንቆማለን፤ ወደ እነርሱም አንወጣም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ ቆዩ ቢሉን በስፍራችን እንቆማለን፥ ወደ እነርሱም አንወጣም። |
እነርሱም የሚሉትን ትሰማለህ፤ ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤”። ስለዚህ ጌዴዎንና አገልጋዩ ፑራ ወደ ጠላት ሰፈር ዳርቻ ወረዱ፤
ነገር ግን ‘ወደ እኛ ኑ’ ቢሉን፥ ወደ እነርሱ እንሄዳለን፤ ይህም እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን የሚያቀዳጀን ለመሆኑ ምልክት ይሆንልናል።”