1 ሳሙኤል 12:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን ብቻ ፍሩ፤ ያደረገላችሁን ድንቅ ነገሮች ተመልክታችሁ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አገልግሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አምልኩት፤ ያደረገላችሁንም ታላላቅ ነገሮች አትርሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብቻ ጌታን ፍሩ፤ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አምልኩት፤ ያደረገላችሁንም ታላላቅ ነገሮች አስቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ያደረገላችሁንም ታላቅ ነገር አይታችኋልና በፍጹም ልባችሁ በእውነት አምልኩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ያደረገላችሁንም ታላቅ ነገር አይታችኋልና በፍጹም ልባችሁ በእውነት አምልኩት። |
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙን የሚፈጽሙትን ሁሉ አስተዋዮች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
በደጃፎቻችሁ መቃኖች ላይ የሚታየው ደም እናንተ የምትኖሩባቸውን ቤቶች ለይቶ የሚያሳይ ምልክት ይሆናል፤ እኔም ደሙን በማይበት ጊዜ አልፌአችሁ እሄዳለሁ፤ በዚህም ዐይነት ግብጻውያንን በመቅሠፍት በምመታበት ጊዜ፥ በእናንተ ላይ ምንም ዐይነት መቅሠፍት አይደርስባችሁም።
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
እግዚአብሔር በሲና ካደረገው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞአብ ምድር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው ተጨማሪ ቃል ኪዳን የሚከተለው ነው፦
ኢያሱ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔርን አክብሩት፤ በፍጹም ቅንነትና በታማኝነት አገልግሉት፤ የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶና በግብጽ ይሰግዱላቸው የነበሩትን ባዕዳን አማልክት አስወግዳችሁ እግዚአብሔርን ብቻ አምልኩ፤