አዳምንም ካስወጣው በኋላ ከዔደን የአትክልት ቦታ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤል የተባሉትን መላእክትንና በየአቅጣጫው እየተገለባበጠ እንደ እሳት የሚንበለበለውን ሰይፍ አኖረ፤ ይህንንም ያደረገው ማንም ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይጠጋ ነው።
1 ሳሙኤል 10:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እነርሱ ፈጠን ብለው በመሄድ ከተሸሸገበት አውጥተው ወደ ሕዝቡ አመጡት፤ ሕዝቡም ሳኦል በትከሻውና በቁመት ከሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ተመለከቱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ሮጠው ከተደበቀበት አመጡት፤ በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜም ቁመቱ ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ሮጠው ከተደበቀበት አመጡት፤ በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜም ቁመቱ ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ሮጦ ከዚያ አመጣው፤ እርሱም በሕዝቡ መካከል አቆመው፤ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ረዥም ነበረ፤ ሕዝቡም ከትከሻው በታች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሮጠው ከዚያ አመጡት፥ እርሱም በሕዝቡ መካከል ቆመ፥ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ከትከሻው ወደ ላይ ከፍ ያለ ቁመተ ረጅም ነበረ። |
አዳምንም ካስወጣው በኋላ ከዔደን የአትክልት ቦታ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤል የተባሉትን መላእክትንና በየአቅጣጫው እየተገለባበጠ እንደ እሳት የሚንበለበለውን ሰይፍ አኖረ፤ ይህንንም ያደረገው ማንም ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይጠጋ ነው።
እግዚአብሔር ግን “የኤሊአብን ቁመት መርዘምና መልከ ቀናነቱን አትይ፤ እኔ እርሱን አልፈለግሁትም፤ እኔ የምፈርደው ሰዎች እንደሚፈርዱት አይደለም፤ ሰው የውጪ መልክን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።
ከጋት ከተማ የመጣ፥ ጎልያድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ግዙፍ ሰው፥ ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጥቶ እስራኤላውያንን መፈታተን ጀመረ፤ የዚያም ሰው ቁመት ሦስት ሜትር ያኽል ነበር፤
ከብንያም ነገድ ቂስ ተብሎ የሚጠራ ታዋቂነት ያለው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር፤ እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጸሮር የልጅ ልጅ ሲሆን ከአፊሐ ጐሣ ወገን የበኮራት ቤተሰብ ነበር።
ቂስም በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሳኦል ተብሎ የሚጠራ ልጅ ነበረው፤ ሳኦልም ከትከሻው ዘለል፥ በቁመት ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ መለል ያለ ነበር፤ በመልከቀናነቱም ከሁሉ ይበልጥ ነበር።