ሶምሶንም ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እየደነፉ መጡበት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አበረታው፤ ክንዱ የታሰሩበት ገመዶች እሳት እንደ ነካቸው የሐር ፈትል ከእጁ ላይ ቀልጠው ወደቁ።
1 ሳሙኤል 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ወደ ጊብዓ በደረሰ ጊዜ የነቢያት ጉባኤ ከሳኦል ጋር ተገናኘ፤ በድንገት የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ላይ ወረደ፤ በዚያን ጊዜም እርሱ ከእነርሱ ጋር ትንቢት መናገር ጀመረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጊብዓ በደረሱ ጊዜ የነቢያቱ ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ወረደበት፤ ከእነርሱም ጋራ ትንቢት ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጊብዓ በደረሱ ጊዜ፥ እነሆ የነቢያቱ ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ተናገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ወረደ፤ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ። |
ሶምሶንም ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እየደነፉ መጡበት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አበረታው፤ ክንዱ የታሰሩበት ገመዶች እሳት እንደ ነካቸው የሐር ፈትል ከእጁ ላይ ቀልጠው ወደቁ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሻን ፊሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሻን ሪሽዓታይምን ድል አደረገው።
ሳሙኤልም በወይራ ዘይት የተሞላውን ቀንድ ወስዶ ዳዊትን በወንድሞቹ ፊት ቀባው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት አደረበት፤ ከዚያም ቀን ጀምሮ ከእርሱ አልተለየም፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ወደ ራማ ተመለሰ።
ለእኔም እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤ የሚያደርግ አንድ ታማኝ ካህን አስነሣለሁ፤ ለእርሱም የጸና ዘር እመሠርትለታለሁ፤ እኔ በቀባሁትም ንጉሥ ፊት ይመላለሳል።