1 ጴጥሮስ 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በሕይወት ባሉትና በሞቱት ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው ለእርሱ መልስ ይሰጡበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው ለእርሱ መልስ ይሰጡበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ። |
“አሁንም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእናንተ ለእስራኤላውያን የምላችሁ ይህ ነው፤ በክፉ ሥራችሁ እያንዳንዳችሁን እቀጣለሁ፤ ስለዚህ ከምታደርጉት ክፋት ተመለሱ፤ አለበለዚያ ኃጢአታችሁ ያጠፋችኋል።
ሀብታሙም ሰው መጋቢውን አስጠርቶ ‘ይህ የምሰማብህ ነገር ምንድን ነው? ከእንግዲህ ወዲህ መጋቢዬ ልትሆን አትችልምና በመጋቢነትህ የሠራህበትን የንብረቴን ሒሳብ አቅርብልኝ’ አለው።
እርሱ በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ሁሉ ላይ በእውነት የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአል፤ ይህንንም ለሁሉም ያረጋገጠው ያን የመረጠውን ሰው ከሞት በማስነሣቱ ነው።”