ዘመንህ ተፈጽሞ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣውን ልጅህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ የእርሱንም መንግሥት አጸናለሁ።
1 ነገሥት 8:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውንም የተስፋ ቃል አጽንተሃል፤ የተናገርከውም ቃል ሁሉ እነሆ ዛሬ ተፈጽሞአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ አጽንተሃል፤ በአፍህ የተናገርኸውን ዛሬም እንደ ሆነው በእጅህ ፈጸምኸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውንም የተስፋ ቃል የጠበቅህ፥ በአፍህ እንደተናገርከው ሁሉ እነሆ ዛሬ በእጅህ ፈጸምከው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ የጠበቅህ፥ በአፍህ ተናግረህ፥ እንደ ዛሬ ቀንም በእጅህ ፈጸምኸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ የጠበቅህ፤ በአፍህ ተናገርህ፤ እንደ ዛሬው ቀንም በእጅህ ፈጸምኸው። |
ዘመንህ ተፈጽሞ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣውን ልጅህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ የእርሱንም መንግሥት አጸናለሁ።
እንዲህም አለ፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ከልባቸው ታማኞች እስከ ሆኑ ድረስ ፍቅሩን የሚያጸና በላይ በሰማይ በታችም በምድር እንደ አንተ ያለ አምላክ የለም!
አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአባቴ ለዳዊት ‘አንተ ታደርግ በነበረው ዐይነት ልጆችህ ታዛዦች ቢሆኑና በፊቴም በቅንነት ቢመላለሱ ሁልጊዜ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም’ ስትል የተናገርከውን የተስፋ ቃል ፈጽም!
ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህና ስለ እውነተኛነትህ የስምህንና የትእዛዞችህን ከፍተኛነት ስላሳየህ ወደ ተቀደሰው ቤተ መቅደስህ እየሰገድኩ ስምህን አመሰግናለሁ።
ማኑሄም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሚስቱን ተከትሎ ሄደ፤ ወደ ሰውየውም ቀርቦ “ከሚስቴ ጋር ተነጋግረህ የነበርከው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም “አዎ! እኔ ነኝ” ሲል መለሰ።