Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 8:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት የሰ​ጠ​ኸ​ውን ተስፋ የጠ​በ​ቅህ፥ በአ​ፍህ ተና​ግ​ረህ፥ እንደ ዛሬ ቀንም በእ​ጅህ ፈጸ​ም​ኸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ አጽንተሃል፤ በአፍህ የተናገርኸውን ዛሬም እንደ ሆነው በእጅህ ፈጸምኸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውንም የተስፋ ቃል የጠበቅህ፥ በአፍህ እንደተናገርከው ሁሉ እነሆ ዛሬ በእጅህ ፈጸምከው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውንም የተስፋ ቃል አጽንተሃል፤ የተናገርከውም ቃል ሁሉ እነሆ ዛሬ ተፈጽሞአል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ የጠበቅህ፤ በአፍህ ተናገርህ፤ እንደ ዛሬው ቀንም በእጅህ ፈጸምኸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 8:24
9 Referencias Cruzadas  

ቤቱ የታ​መነ ይሆ​ናል፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በፊቴ ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ዙፋ​ኑም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል።”


እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ዕድ​ሜ​ህም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ፥ ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣ​ውን ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ ።


ማኑ​ሄም ተነ​ሥቶ ሚስ​ቱን ተከ​ተለ፤ ወደ ሰው​ዬ​ዉም መጥቶ፥ “ከሚ​ስቴ ጋር የተ​ነ​ጋ​ገ​ርህ አንተ ነህን?” አለው። መል​አ​ኩም፥ “እኔ ነኝ” አለ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በላይ በሰ​ማይ፥ በታ​ችም በም​ድር አን​ተን የሚ​መ​ስል አም​ላክ የለም፤ በፍ​ጹም ልቡ በፊ​ትህ ለሚ​ሄድ ባሪ​ያህ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥


አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ፦ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆ​ችህ በፊቴ ይሄዱ ዘንድ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ፥ በፊቴ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ ሰው ከአ​ንተ አይ​ጠ​ፋም ብለህ ለአ​ባ​ቴ ለ​ዳ​ዊት ተስፋ የሰ​ጠ​ኽ​ውን ጠብቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከተ​ና​ገ​ረው መል​ካም ነገር ሁሉ ተፈ​ጸመ እንጂ ምንም አል​ቀ​ረም።


አንተ መቀ​መ​ጤ​ንና መነ​ሣ​ቴን ታው​ቃ​ለህ። የል​ቤን ዐሳብ ሁሉ ከሩቁ ታስ​ተ​ው​ላ​ለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios