1 ነገሥት 8:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤ “አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስን ለመሥራት ዐቅዶ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ ለመሥራት በልቡ ዐስቦ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ቤተ መቅደስን ለመሥራት ዐቅዶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቴም ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ይሠራ ዘንድ በልቡ አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቴም ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ይሠራ ዘንድ በልቡ አሰበ። |
ሁሉም በተሰበሰቡ ጊዜ ዳዊት ተነሥቶ፥ እንዲህ አለ፦ “ወገኖቼ ሆይ፥ አድምጡኝ፤ ለአምላካችን የእግር ማሳረፊያ ይሆን ዘንድ የተቀደሰው ታቦት የሚያርፍበት ቤት ለመሥራት ፈልጌ ነበር፤ ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ማሠሪያ የሚሆነውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅቼአለሁ፤