1 ነገሥት 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሾማቸው ባለሥልጣኖች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፥ እነርሱም፦ ዓዛርያስ የተባለው የሳዶቅ ልጅ፦ ካህን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዋና ዋናዎቹ ሹማምቱም እነዚህ ነበሩ፤ የሳዶቅ ልጅ ዓዛርያስ፣ ካህን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሾማቸው ባለ ሥልጣኖች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፤ እነርሱም፦ ዓዛርያስ የተባለው የሳዶቅ ልጅ፦ ካህን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነበሩትም አለቆች እነዚህ ናቸው፥ የሳዶቅ ልጅ ካህኑ ዓዛርያስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የነበሩትም አለቆች እነዚህ ናቸው፤ የሳዶቅ ልጅ ካህኑ ዓዛርያስ፥ |
በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር እያንዳንዱ ሰው በቤተ ክርስቲያን የተለያየ አገልግሎት እንዲኖረው አድርጓል፤ በዚህም መሠረት በመጀመሪያ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛ ነቢያትን፥ ሦስተኛ መምህራንን ሾሞአል። ቀጥሎም ተአምራት የሚያደርጉትን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፥ ሰዎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፥ አስተዳዳሪዎችንና በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩትን ሰዎች መድቦአል።