ሰሎሞን ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ ያነጋገረው መሆኑን ተገነዘበ፤ ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆሞ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ከዚህም በኋላ ባለሟሎቹ ለሆኑ ባለሥልጣኖች ሁሉ ግብዣ አደረገ።
1 ነገሥት 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ሁለት ጋለሞታዎች መጥተው በሰሎሞን ፊት ቀረቡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ሁለት ዝሙት ዐዳሪዎች ወደ ንጉሡ መጥተው ከፊቱ ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ቀን ሁለት ጋለሞታዎች መጥተው በሰሎሞን ፊት ቀረቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜም ሁለት ጋለሞታዎች ሴቶች ወደ ንጉሡ መጥተው ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ሁለት ጋለሞቶች ሴቶች ወደ ንጉሡ መጥተው በፊቱ ቆሙ። |
ሰሎሞን ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ ያነጋገረው መሆኑን ተገነዘበ፤ ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆሞ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ከዚህም በኋላ ባለሟሎቹ ለሆኑ ባለሥልጣኖች ሁሉ ግብዣ አደረገ።
ከእነርሱም አንደኛይቱ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ሆይ! ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት አብረን ስንኖር በዚያው በምንኖርበት ቤት ወንድ ልጅ ወለድኩ፤
ከዚህ በኋላ የነዌ ልጅ ኢያሱ ከሺጢም ሰፈር ሁለት ሰላዮችን ላከ፤ እነርሱም የከነዓንን ምድር በተለይም የኢያሪኮን ከተማ በምሥጢር ሰልለው እንዲመለሱ አዘዛቸው፤ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ “ረዓብ” ተብላ ወደምትጠራ ወደ አንዲት ሴትኛ ዐዳሪ ቤት ገብተው ዐደሩ።