ሴቲቱም ዛፉ የሚያምር፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመዥና ጥበብን የሚያስገኝ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ለባሏም ከፍሬው ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
1 ነገሥት 21:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቱም ኤልዛቤል ወደ እርሱ ቀርባ “እንደዚህ ያበሳጨህ ነገር ምንድን ነው? ስለምንስ ምግብ አትበላም?” ስትል ጠየቀችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚስቱ ኤልዛቤልም ወደ እርሱ ገብታ፣ “እስከዚህ የተበሳጨኸው፣ ምግብስ የማትበላው ለምንድን ነው?” ብላ ጠየቀችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም መልእክተኞች ተመልሰው፦ የአዴር ልጅ እንዲህ ይላል፦ “ቀድሞ ብርህንና ወርቅህን ሴቶችህንና ልጆችህንም ትሰጠኛለህ ብዬ ልኬብህ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም መልእክተኞች ተመልሰው መጥተው እንዲህ አሉት፥ “ወልደ አዴር እንዲህ ይላል፦ ቀድመህ ብርህንና ወርቅህን፥ ሚስቶችህንና ልጆችህንም ላክልኝ ብዬ ልኬብህ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም መልእክተኞች ተመልሰው፦ ወልደ አዴር እንዲህ ይላል፦ ቀድሞ ብርህንና ወርቅህን ሴቶችህንና ልጆችህንም ትሰጠኛለህ ብዬ ልኬብህ ነበር፤ |
ሴቲቱም ዛፉ የሚያምር፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመዥና ጥበብን የሚያስገኝ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ለባሏም ከፍሬው ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
ዮናዳብ አምኖንን “አንተ የንጉሥ ልጅ ሆነህ ሳለ በየቀኑ ሰውነትህ ጠውልጎ የማይህ ስለምንድን ነው? እስቲ ንገረኝ” ሲል ጠየቀው። አምኖንም “የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን ስለ ወደድኩ ነው” ሲል መለሰለት።
አክዓብ፥ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኃጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቊጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም፤
ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር።
ስለዚህ እርስዋ “በእነዚያ ነቢያት ላይ ያደረግኸውን እኔም ነገ ልክ በአሁኑ ሰዓት በአንተ ላይ ሳላደርግብህ ብቀር አማልክት በሞት ይቅሠፉኝ!” ስትል ወደ ኤልያስ የዛቻ መልእክት ላከች።
በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ ሁለንተናውን ለኃጢአት አሳልፎ የሸጠ አክዓብን የሚምስል ማንም አልነበረም፤ ይህን ሁሉ ለማድረግ የተገደደው ሚስቱ ኤልዛቤል ወደ ክፋት ስለ መራችው ነው፤
አክዓብ፥ የእዝራኤላዊው ናቡቴ “ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም!” ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም።
እርሱም “እኔን ያበሳጨኝ ከናቡቴ ያገኘሁት መልስ ነው፤ ይኸውም የእርሱን የወይን ተክል ቦታ እንድገዛ ወይም ከፈለገ ልዋጩን እንድሰጠው ብጠይቀው የወይን ተክል ቦታውን ‘በምንም ዐይነት አልሰጥህም’ ብሎ አናደደኝ” ሲል መለሰላት።
ስለዚህም “አንዳች የልብ ሐዘን ቢደርስብህ ነው እንጂ ሳትታመም እንዴት ይህን ያኽል በፊትህ የሐዘን ምልክት ይታያል?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም እጅግ በመፍራት፥
ከዚህም በኋላ አስቴር ከቤተ መንግሥቱ ጃንደረቦች መካከል በተለይ እርስዋን እንዲያገለግል ንጉሡ የመደበላትን ሀታክ የተባለውን ጠርታ ወደ መርዶክዮስ ዘንድ ሄዶ ምን እንደ ደረሰበት እንዲጠይቀው ላከችው።