ከዚህ በኋላ አቤሜሌክ አብርሃምን ጠርቶ፦ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ይህን በደል ያመጣህብን ምን ያስቀየምኩህ ነገር ቢኖር ነው? አንተ ያደረግህብኝን ነገር ከቶ ማንም ሰው አያደርገውም፤
1 ነገሥት 15:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ ኃጢአት በመሥራት የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በአባቱ መንገድ በመሄድ፣ አባቱ የሠራውንና እስራኤልም እንዲሠሩ ያደረገውን ኀጢአት በመሥራት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በፊት እንደነበረው እንደ አባቱ ኃጢአት በመሥራት የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፤ በአባቱም መንገድ እስራኤልንም ባሳተበት ኀጢአት ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፤ በአባቱም መንገድ እስራኤልንም ባሳተበት ኀጢአት ሄደ። |
ከዚህ በኋላ አቤሜሌክ አብርሃምን ጠርቶ፦ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ይህን በደል ያመጣህብን ምን ያስቀየምኩህ ነገር ቢኖር ነው? አንተ ያደረግህብኝን ነገር ከቶ ማንም ሰው አያደርገውም፤
ይህም የሆነበት ምክንያት ኢዮርብዓም ራሱ በሠራው ኃጢአትና የእስራኤልም ሕዝብ ኃጢአት እንዲሠሩ በማድረግ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቊጣ ስላነሣሣ ነው።
ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ባዕሻ ራሱ ኃጢአት በመሥራትና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራት እግዚአብሔርን አሳዘነ።
ይህ የሆነበት ምክንያት በሠራው ኃጢአት እግዚአብሔርን በማሳዘኑ ነው፤ እርሱ ራሱ በሠራው ኃጢአትና እስራኤልንም ወደ ኃጢአት በመምራቱ ምክንያት ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ኢዮርብዓም እግዚአብሔርን አስቈጥቶአል።
እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻና በቤተሰቡ ላይ ያን የትንቢት ቃል የተናገረበት ምክንያት፥ ባዕሻ በፈጸመው ኃጢአት እግዚአብሔርን ስላሳዘነ ነበር፤ ባዕሻ እግዚአብሔርን ያስቈጣውም ከእርሱ ፊት የነበረው ንጉሥ ባደረገው ዐይነት ስለ ሠራው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን የኢዮርብዓምንም ቤተሰብ ሁሉ በመግደሉ ጭምር ነው።
እስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራታችሁ ቊጣዬን ስለ አነሣሣህ ቤተሰብህን እንደ ናባጥ እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ቤተሰብና እንደ አኪያ ልጅ እንደ ንጉሥ ባዕሻ ቤተሰብ ለማጥፋት የተጋለጠ ይሆናል።
እርሱም የአባቱን የአክዓብን፥ የእናቱን የኤልዛቤልንና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት በደል ሠራ።
“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤
እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤል አሠርቶት የነበረውን የማምለኪያ ቦታ ኢዮስያስ አፈራርሶ ጣለ፤ መሠዊያውን ነቅሎ፥ የተሠራበትን ድንጋይ ሁሉ ሰባብሮ በማድቀቅ እንደ ትቢያ አደረገው፤ የአሼራንም ምስል በእሳት አቃጠለ፤
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ሞሌክ ለተባለው ጣዖት መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በሄኖም ሸለቆ ውስጥ ለበዓል ጣዖት መሠዊያ ሠርተዋል፤ እኔ ይህን እንዲያደርጉ አላዘዝኳቸውም የይሁዳንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ለመምራት ይህን ያደርጋሉ ብዬ አልጠበቅሁም ነበር።”
አንተ በምትበላው ምግብ ምክንያት ለወንድምህ እንቅፋት ከሆንክ በፍቅር የምትኖር አይደለህም፤ ስለዚህ ክርስቶስ የሞተለትን ሰው በምትበላው ምግብ ምክንያት እንዲጠፋ አታድርግ።