1 ነገሥት 13:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በገበታም ቀርበው ሳሉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሽማግሌው ነቢይ መጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማእድ ተቀምጠው ሳሉ፣ የእግዚአብሔር ቃል መልሶ ወደ አመጣው ወደ ሽማግሌው ነቢይ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገበታም ቀርበው ሳሉ የጌታ ቃል ወደ መለሰው ነቢይ መጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማዕድም ተቀምጠው ሳሉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ መለሰው ነቢይ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማዕድም ተቀምጠው ሳሉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ መለሰው ነቢይ መጣ፤ |
ከይሁዳ ለመጣው የእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃል አላከበርክም።
በፍርድ ቀን ብዙዎች፥ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።
እርሱም ይህን የተናገረው፥ ከራሱ አመንጭቶ አልነበረም፤ ነገር ግን በዚያን ዓመት እርሱ የካህናት አለቃ ስለ ነበረ፥ ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ መሞት እንደሚገባው ሲያመለክት ይህን ትንቢት ተናገረ።
ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝና ምሥጢርንም ሁሉ ብረዳ፥ ዕውቀትም ሁሉ ቢኖረኝ፥ ተራራን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያፈልስ እምነትም ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።