1 ነገሥት 12:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዐይነት ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራቸውም ምስሎች በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃ ምስሉ መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም በቤትኤል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሁዳ እንደሚደረገው ሁሉ ኢዮርብዓምም በስምንተኛው ወር ዐሥራ ዐምስተኛው ቀን በዓል እንዲሆን ወሰነ፤ በመሠዊያውም ላይ መሥዋዕት አቀረበ። ለሠራቸው ጥጆች መሥዋዕት በማቅረብም እንዲህ ያለውን ድርጊት በቤቴል ፈጸመ። በማምለኪያ ኰረብቶች ላይ ላሠራቸው አብያተ ጣዖታት በቤቴል ካህናቱን መደበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዓይነት ስምንተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራቸውም ምስሎች በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃው ምስል መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም በቤትኤል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮርብዓምም በስምንተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በይሁዳ እንደሚደረግ በዓል ያለ በዓል አደረገ፤ ለሠራቸውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ በቤቴል ወደ ሠራው መሠዊያ ወጣ፤ ለኮረብታ መስገጃዎችም የመረጣቸውን እነዚያን ካህናት በቤቴል አኖራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስምንተኛው ወር በዐሥራ አምስተኛውም ቀን በይሁዳ እንደሚደረግ በዓል ያለ በዓል አደረገ፤ በመሠዊያውም ላይ ሠዋ፤ ለሠራቸውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ እንዲሁ በቤቴል አደረገ፤ ለኮረብታ መስገጃዎችም የመረጣቸውን ካህናት በቤቴል አኖራቸው። |
ይህም ሁሉ ሆኖ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ከሚያደርገው ክፉ ነገር ሁሉ አልተመለሰም፤ ይልቁንም እርሱ በሠራቸው መሠዊያዎች የሚያገለግሉ ከሌዊ ዘር ውጪ ከሆኑ ቤተሰቦች መምረጡን ቀጥሎ ካህን ለመሆን ከፈለገ ማንኛውንም ሰው ይሾመው ነበር፤
ንጉሥ ሰሎሞንና መላው የእስራኤል ሕዝብ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ተሰበሰቡ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር የማይቻል ብዙ በግና የቀንድ ከብት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።
ነገሥታቱ የቤተ መንግሥታቸውን መድረኮችና መቃኖች ወደ ቤተ መቅደሴ መድረኮችና መቃኖች አስጠግተው ስለ ሠሩ፥ የእኔን ቤትና የእነርሱን ቤት የሚለይ አንድ ግንብ ብቻ ሆኖአል፤ በፈጸሙትም አጸያፊ ድርጊት ሁሉ ቅዱስ ስሜን አሰድበዋል፤ ከዚህም የተነሣ በቊጣዬ አጠፋኋቸው።
ይህ ሚካ የተባለ ሰው የራሱ የሆነ የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ በርከት ያሉ ጣዖቶች አንድ ኤፉድ ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው፤