ቀጥላም “ ‘ሣራ ለአብርሃም ልጅ ወልዳ ታጠባለች’ ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር? አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድኩለት” አለች።
1 ነገሥት 11:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ገኑባት ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ እርሱንም ንግሥቲቱ ወስዳ በቤተ መንግሥት አሳደገችው፤ ከንጉሡም ወንዶች ልጆች ጋር አብሮ ኖረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጣፍኔስም እኅት ጌንባት የተባለውን ልጅ ወለደችለት፤ ጣፍኔስ በፈርዖን ቤት አሳደገችው፤ ጌንባትም ከፈርዖን ልጆች ጋራ አደገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ገኑባት ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ እርሱንም ንግሥቲቱ ወስዳ በቤተ መንግሥት አሳደገችው፤ ከንጉሡም ወንዶች ልጆች ጋር አብሮ ኖረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቴቄምናስ እኅት ወንድ ልጅ ጌንባትን ለአዴር ወለደችለት፤ ቴቄምናስም በፈርዖን ልጆች መካከል አሳደገችው፤ ጌንባትም በፈርዖን ልጆች መካከል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቴቄምናስ እኅት ጌንባትን ወለደችለት፤ ቴቄምናስም በፈርዖን ቤት አሳደገችው፤ ጌንባትም በፈርዖን ቤት በፈርዖን ልጆች መካከል ነበረ። |
ቀጥላም “ ‘ሣራ ለአብርሃም ልጅ ወልዳ ታጠባለች’ ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር? አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድኩለት” አለች።
ሀዳድ በግብጽ ሳለ የንጉሥ ዳዊትንና የሠራዊቱን አዛዥ የኢዮአብን መሞት በሰማ ጊዜ “ወደ አገሬ ተመልሼ እንድሄድ አሰናብተኝ” ሲል ንጉሡን ጠየቀ።
ጡት ካስጣለችውም በኋላ ወደ ሴሎ ይዛው ወጣች፤ ከእርሱም ጋር የሦስት ዓመት ኰርማ ዐሥር ኪሎ ዱቄትና አንድ አቁማዳ ሙሉ የወይን ጠጅ ይዛ ሄደች፤ ሳሙኤልንም ገና በልጅነቱ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው፤