1 ነገሥት 10:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሦስት መቶ ታናናሽ ጋሻዎችን አሠርቶ እያንዳንዱን በሁለት ኪሎ ያኽል ወርቅ አስለበጠው፤ እነዚህንም ሁሉ “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ አኖራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት መቶ ትንንሽ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእያንዳንዱ ጋሻ የገባው ጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት ምናን ነበር። ንጉሡም ጋሻዎቹን የሊባኖስ ደን በተባለው ቤተ መንግሥት ውስጥ አኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ሦስት መቶ ታናናሽ ጋሻዎችን አሠርቶ እያንዳንዱን በሁለት ኪሎ ያኽል ወርቅ አስለበጠው፤ እነዚህንም ሁሉ “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ አኖራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥፍጥፍም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በአንዱም ጋሻ የገባው ወርቅ ሦስት ምናን ነው፤ ንጉሡም የሊባኖስ ዱር በተባለው ቤት ውስጥ አኖራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጥፍጥፍም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በአንዱም ጋሻ የገባው ወርቅ ሦስት ምናን ነበረ፤ ንጉሡም የሊባኖስ ዱር በተባለው ቤት ውስጥ አኖራቸው። |
“የሊባኖስ ደን” ተብሎ የተጠራው አዳራሽ ርዝመቱ አርባ አራት ሜትር፥ ወርዱ ኻያ ሁለት ሜትር፥ ቁመቱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር፤ አዳራሹም በእያንዳንዱ ረድፍ ዐሥራ አምስት ሆነው በሦስት ረድፍ የቆሙ አርባ አምስት ምሰሶዎች ነበሩት፤ በምሰሶዎቹም ላይ የተጋደሙ፥ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠሩ ሠረገሎችና በየመካከላቸው የገቡ ሳንቃዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም በላይ በምሰሶዎቹ የተደገፉ ዕቃ ቤቶች ነበሩ፤ የእነዚህም ዕቃ ቤቶች ጣራ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር፤
ስለዚህ ንጉሥ ሺሻቅ በድል አድራጊነት ወደ ኢየሩሳሌም ገብቶ፥ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ፥ ንጉሥ ሰሎሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ፤