1 ነገሥት 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ከታላላቅና ከተራ ነጋዴዎች ከሚገባው ቀረጥ፣ መላው የዐረብ ነገሥታት ከሚያስገቡትና አገረ ገዦች ከሚሰበስቡት ግብር ሌላ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኽንም፥ ግብር የሚያስገብሩ ሰዎች፥ ነጋዴዎችም፥ በዙሪያው ያሉ ነገሥታትም ሁሉ፥ የምድርም ሹሞች ከሚያወጡት ሌላ ነው። |
ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ ስድስተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ እግዚአብሔር በነቢዩ አማካይነት በሐጌ ተናገረ የተናገረውም የይሁዳ ገዢ ለነበረው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤልና ሊቀ ካህናት ለነበረው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ ነው።
አጋር በዐረብ አገር ለሚገኘው ለሲና ተራራ ምሳሌ ነበረች፤ ስለዚህ ከአሁኒቱ ኢየሩሳሌም ጋር ትመሳሰላለች፤ እርስዋ ከነልጆችዋ በባርነት የምትገኝ ናት።