1 ዮሐንስ 4:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዓለም እኛ የምንኖረው ልክ ክርስቶስ እንደሚኖረው እንደ መሆኑ ፍቅራችን ፍጹም ቢሆን በፍርድ ቀን ያለ ፍርሀት በፊቱ ለመቅረብ ሙሉ መተማመን ይኖረናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ዓለም እርሱን እንመስላለንና፤ በፍርድ ቀን ድፍረት ይኖረን ዘንድ፣ ፍቅር በዚህ ዐይነት በመካከላችን ፍጹም ሆኗል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍርድ ቀን ድፍረት እንዲኖረን ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ ምክንያቱም እርሱ እንደሆነ እኛ ደግሞ በዚህ ዓለም እንዲሁ ነን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና። |
ስለዚህ ተማሪ እንደአስተማሪው፥ አገልጋይም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። የቤቱን ጌታ ‘ብዔልዜቡል’ ብለው ከጠሩት ቤተሰቦቹንማ ከዚህ በከፋ ስም እንዴት አይጠሩአቸውም!
ይህም የሆነበት ምክንያት አስቀድሞ ያወቃቸው ልጁን እንዲመስሉና ልጁም ከብዙ ወንድሞች መካከል በኵር እንዲሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ ወሰነ ነው።
እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው።
ነገር ግን ለእግዚአብሔር ቃል የሚታዘዝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር ፍጹም ነው፤ በእውነት በእርሱ የምንኖር መሆናችንም የሚታወቀው በዚሁ ነው፤
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ! በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ዓለም እግዚአብሔርን ስላላወቀ እኛንም አያውቀንም።