1 ዮሐንስ 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት አለን” እያልን በጨለማ የምንኖር ከሆንን እንዋሻለን፤ በቃላችንም ሆነ በሥራችን እውነት የለም ማለት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ጋራ ኅብረት አለን እያልን በጨለማም ብንመላለስ፣ እንዋሻለን፤ እውነቱንም አናደርግም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን እያልን በጨለማ ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ |
በፍርድ ቀን ብዙዎች፥ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
ሆኖም እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ እኔ አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንኩ ነበር፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።
እንዲህም ዐይነቱ ትምህርት የሚመነጨው በግብዝነት፥ ሐሰትን ሲናገሩ በጋለ ብረት እንደ ተተኮሰ ያኽል ሆኖ የደነዘዘ ኅሊናቸው ከማይወቅሳቸው ሰዎች ነው።
ነገር ግን “አንተ እምነት አለህ፤ እኔም መልካም ሥራ አለኝ” የሚል ቢኖር፥ “እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም በሥራዬ እምነቴን አሳይሃለሁ” እለዋለሁ።
ከእኛ ጋር አንድነት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተም እንነግራችኋለን። አንድነታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።