La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 7:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሚስት በሰውነቷ ላይ ሥልጣን የላትም፤ በእርስዋ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያለው ባልዋ ነው። እንዲሁም ባል በሰውነቱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ በእርሱ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያላት ሚስቱ ነች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሚስት በራሷ አካል ላይ ሥልጣን የላትም፤ ባሏ እንጂ። እንዲሁም ባል በራሱ አካል ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሚስቱ እንጂ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሚስት በገዛ ሰውነቷ ላይ ሥልጣን የላትም፤ ሥልጣን ለባሏ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሰውነቱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሚስት በራ​ስዋ አካል ሥል​ጣን የላ​ትም፤ ሥል​ጣን ለባ​ልዋ ነው እንጂ፤ እን​ዲ​ሁም ባል በራሱ አካል ሥል​ጣን የለ​ውም፤ ሥል​ጣን ለሚ​ስቱ ነው እንጂ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፥ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 7:4
5 Referencias Cruzadas  

“ሳታመነዝሪና ሰውነትሽን ለማንኛውም ወንድ ሳትሰጪ እኔን እየጠበቅሽ ለብዙ ጊዜ መቈየት አለብሽ፤ እኔም ለአንቺ እንዲሁ አደርግልሻለሁ” ብዬ ነገርኳት።


“እኔ ግን፥ ‘አንድ ሰው በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሴት ቢያገባ አመነዘረ’ እላችኋለሁ።”


ባል ለሚስቱ ማድረግ የሚገባውን የጋብቻ መብትዋን አይከልክላት፤ እንዲሁም ሚስት ለባልዋ ማድረግ የሚገባትን የጋብቻ መብቱን አትከልክለው።


በጸሎት ለመትጋት ሁለታችሁም ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር በመለያየት አንዱ የሌላውን የጋብቻ መብት አይከልክል። በዚህም ምክንያት ራሳችሁን መቈጣጠር አቅቶአችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ።