1 ቆሮንቶስ 16:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉን በፍቅር አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን። |
አንተ በምትበላው ምግብ ምክንያት ለወንድምህ እንቅፋት ከሆንክ በፍቅር የምትኖር አይደለህም፤ ስለዚህ ክርስቶስ የሞተለትን ሰው በምትበላው ምግብ ምክንያት እንዲጠፋ አታድርግ።
ወንድሞች ሆይ! የእስጢፋኖስ ቤተሰብ በአካይያ አገር የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደ ሆኑና ምእመናንን ለማገልገል ራሳቸውን አሳልፈው እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ።
አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ ደስ የሚያሰኝ ዜና ነገረን፤ እንዲሁም እናንተ ዘወትር በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ እናንተን ለማየት የምንናፍቃችሁን ያኽል እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁ ነገረን።
ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ማመስገንም ተገቢያችን ነው፤ የምናመሰግነውም እምነታችሁ ይበልጥ እያደገና የእያንዳንዳችሁ የእርስ በርስ ፍቅር እየጨመረ በመሄዱ ነው።
ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የተከበረ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን እግዚአብሔር ስለሚፈርድባቸው ባልና ሚስት ታማኝነትን በማጒደል ጋብቻን አያርክሱ።