ሁላቸውም አንድ ክፍል ብቻ ቢሆን ኖሮ ሙሉ አካል የት በተገኘ ነበር!
ሁሉም አንድ ብልት ቢሆን ኖሮ አካል ከየት ይገኝ ነበር?
ሁሉም አንድ የአካል ክፍል ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ?
የአካል ክፍሉ አንድ ቢሆን ኖሮ አካል የት በተገኘ ነበር?
ሁሉም አንድ ብልት ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ?
አንድ አካል የተሠራው ከብዙ የአካል ክፍሎች እንጂ ከአንድ የአካል ክፍል ብቻ አይደለም!
አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ፈለገው እያንዳንዱን የአካል ክፍል በአካል ውስጥ ተገቢ ስፍራውን ይዞ እንዲገኝ አድርጎታል።
አሁን ግን ብዙ የአካል ክፍሎች ቢኖሩም አካል ግን አንድ ብቻ ነው።