አንድ ሰው ብዙ የአካል ክፍሎች አሉት፤ የአካል ክፍሎች ብዙዎች ሆነው ሳሉ የሚገኙት በዚያው በአንዱ አካል ነው። እንዲሁም ክርስቶስ ብዙ የሰውነት ክፍሎች እንዳሉት እንደ አንድ አካል ነው።
1 ቆሮንቶስ 12:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ አካል የተሠራው ከብዙ የአካል ክፍሎች እንጂ ከአንድ የአካል ክፍል ብቻ አይደለም! አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካል የተሠራው ከብዙ ብልቶች እንጂ ከአንድ ብልት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካል ብዙ የአካል ክፍሎች እንጂ አንድ የአካል ክፍል አይደለምና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአካላችንም ክፍሉ ብዙ ነው እንጂ አንድ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አካል ብዙ ብልቶች እንጂ አንድ ብልት አይደለምና። |
አንድ ሰው ብዙ የአካል ክፍሎች አሉት፤ የአካል ክፍሎች ብዙዎች ሆነው ሳሉ የሚገኙት በዚያው በአንዱ አካል ነው። እንዲሁም ክርስቶስ ብዙ የሰውነት ክፍሎች እንዳሉት እንደ አንድ አካል ነው።