ካህኑም ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ የራስዋንም ጠጒር ይፍታ፤ የቅናቱንም የእህል ቊርባን በእጅዋ ላይ ያስቀምጥ፤ በእጁም እርግማንን የሚያመጣ መራራ ውሃ ይያዝ።
1 ቆሮንቶስ 11:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴት ግን ጠጒር የተሰጣት ራሷን ልትሸፍንበት ስለ ሆነ ጠጒርዋን ብታስረዝም ለእርስዋ ክብርዋ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴት ግን ጠጕሯን ብታስረዝም ክብሯ አይደለምን? ረዥም ጠጕር የተሰጣት መጐናጸፊያ እንዲሆናት ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር አይደለምን? ምክንያቱም ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሴት ግን ጠጕርዋን ብታሳድግ ክብርዋ ነው፤ ለሴት ጠጕርዋ እንደ ቀጸላ ሆኖ ተሰጥቶአታልና። |
ካህኑም ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ የራስዋንም ጠጒር ይፍታ፤ የቅናቱንም የእህል ቊርባን በእጅዋ ላይ ያስቀምጥ፤ በእጁም እርግማንን የሚያመጣ መራራ ውሃ ይያዝ።