ሶፎንያስ 3:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከበዓሉ ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፤ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለ ክብረ በዓላት መተጓጐል የተከዝሽበትን፣ የስድብሽን ሸክም፤ ከአንቺ አስወግዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በበዓል ቀን እንደሚደረገው የደስታ ስሜት እንዲሰማሽ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ኀፍረት አይደርስብሽም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጉባኤው ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፣ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጉባኤው ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፥ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር። |
ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ድንግሎችዋም ተጨነቁ እርሷም በምሬት አለች።
ዛይ። ኢየሩሳሌም በጭንቀትዋና በመከራዋ ወራት ከጥንት ጀምሮ የነበረላትን የከበረን ነገር ሁሉ አሰበች፥ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት በመፍረስዋም ሳቁ።
ከሕዝቦች አወጣቸዋለሁ፥ ከአገሮች እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች ላይ፥ በፈሳሾች አጠገብ፥ በምድሪቱም መኖሪያ በሚሆኑ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።
ጌታም እንዲህ አለው፦ በከተማይቱ መካከል፥ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኩሰት ሁሉ በሚተክዙና በሚያለቅሱ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክትን አድርግ።
በዚያ ዘመን እሰበስባችኋለሁ፥ በሰበሰብኳችሁም ጊዜ፤ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።