ሶፎንያስ 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን ኢየሩሳሌም እንዲህ ይባልላታል፦ “ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን እንዲህ ይሏታል፤ “ጽዮን ሆይ፤ አትፍሪ፤ እጆችሽም አይዛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ስለ ኢየሩሳሌም እንደዚህ ይባልላታል፤ “የጽዮን ከተማ ሆይ! አትፍሪ! ክንዶችሽም አይዛሉ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም፦ ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም፦ ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ። |
በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል፤ ጌታ ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ይባላል።
የምሥራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፥ ከፍ ወደለው ተራራ ውጪ፤ የምሥራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ድምፅሽን በኃይል አንሺ፤ አንሺ፥ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች፦ እነሆ፥ አምላካችሁ! ብለሽ ንገሪ።
የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ በረከት መሆን እንድትችሉ አድናችኋለሁ፤ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።