ጌታም ኤልያስን “ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም” አለው፤ ከዚህ በኋላ ጌታ በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኰረብቶችን ሰነጣጠቀ፤ አለቶችንም ሰባበረ፤ ጌታ ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ ጌታ ግን በምድሪቱ ነውጥ ውስጥ አልነበረም።
ዘካርያስ 6:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልአኩም መልሶ፦ “በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙበት ስፍራ የሚወጡ እነዚህ አራቱ የሰማይ ነፋሳት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ አራቱ ቆመው ከነበሩበት ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት የወጡ የሰማይ መናፍስት ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “እነዚህ አራቱ ነፋሳት ናቸው፤ ቆመው ከሚያገለግሉበት ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት አሁን ገና መውጣታቸው ነው” አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልአኩም መልሶ፦ እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙበት ስፍራ የሚወጡ አራቱ የሰማይ ነፋስት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልአኩም መልሶ፦ እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙበት ስፍራ የሚወጡ አራቱ የሰማይ ነፋስት ናቸው። |
ጌታም ኤልያስን “ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም” አለው፤ ከዚህ በኋላ ጌታ በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኰረብቶችን ሰነጣጠቀ፤ አለቶችንም ሰባበረ፤ ጌታ ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ ጌታ ግን በምድሪቱ ነውጥ ውስጥ አልነበረም።
ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ጌታ የሚለውን ስማ! ጌታ በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፥ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤
ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፥ ወደ እነዚያም ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች ተሰድደው ያልደረሱበት ሕዝብ አይገኝም።
እንዲህም አለኝ፦ “ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር የሰው ልጅ ሆይ፥ ነፋሱንም እንዲህ በለው፦ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ፥ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ በሕይወት እንዲኖሩ በእነዚህ በተገደሉት ላይ እፍ በልባቸው።’”
የዚህን የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን አይተው ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የጌታ ዐይኖች ናቸው።”
ከዚህም በኋላ በአራቱ የምድር ማዕዘን የቆሙ አራት መላእክት አየሁ፤ እነርሱም ነፋስ በምድር ላይም ቢሆን ወይም በባሕር ላይ ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳት ያዙ።