La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘካርያስ 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም፦ “ምንድን ናት?” አልኩት። እርሱም፦ “ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት” አለኝ። ደግሞም፦ “ይህ ነው በምድር ሁሉ ያለ የእነርሱ በደል” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም፣ “ምንድን ነው?” አልሁት። እርሱም፣ “የኢፍ መስፈሪያ ነው” አለኝ። ቀጥሎም “ይህ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ያለው የሕዝቡ በደል ነው” አለኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔም “ይህ ነገር ምንድን ነው?” አልኩት። እርሱም “በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚሠራውን ኃጢአት የሚያመለክት ቅርጫት ነው” አለኝ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።

Ver Capítulo



ዘካርያስ 5:6
8 Referencias Cruzadas  

ትክክለኛም ሚዛን፥ ትክክለኛም መመዘኛ፥ ትክክለኛም የኢፍ መስፈሪያ፥ ትክክለኛም የኢን መስፈሪያ ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


ችግረኛውን የምትረግጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ ይህን ስሙ፤


እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህልን እንድንሸጥ መባቻው መቼ ያልፋል? ስንዴውንም ለሽያጭ ገበያ ለማቅረብ ሰንበት መቼ ያበቃል? የኢፍ መስፈሪያውንም እናሳንሳለን፥ ሰቅሉንም እናበዛለን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እናታልላለን፥


ድሀውን በብር ችግረኛውንም በአንድ ጥንድ ጫማ እንገዛለን፥ የስንዴውን ገለባ እንሸጣለን።”


በክፉ ቤት የክፋት መዝገብ፥ አስጸያፊ ሐሰተኛ መስፈሪያ አሁንም አለን?


በዚያን ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት በዓመፅና በማታለል የሚሞሉትን እቀጣለሁ።


ከዚያም የእርሳሱን መክሊት አነሡት፥ እነሆም፥ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር።