እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ዐይኖችህን ወደ ሰሜን መንገድ አንሣ። እኔም ዐይኖቼን ወደ ሰሜን መንገድ አነሣሁ፥ እነሆም በመሠዊያው በር በሰሜን በኩል፥ በመግቢያው የቅናቱ ጣዖት ነበረ።
ዘካርያስ 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ “ዐይኖችህን አንሣ፥ ይህችም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክ ወደ እኔ መጥቶ፣ “ወደ ላይ ተመልከት፤ ይህ የሚመጣው ምን እንደ ሆነ እይ” አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም እንደገና ወደ እኔ መጥቶ “የሚመጣው ነገር ምን እንደ ሆነ ተመልከት!” አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ ዓይኖችህን አንሣ፥ ይህችንም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ ዓይኖችህን አንሣ፥ ይህችንም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ አለኝ። |
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ዐይኖችህን ወደ ሰሜን መንገድ አንሣ። እኔም ዐይኖቼን ወደ ሰሜን መንገድ አነሣሁ፥ እነሆም በመሠዊያው በር በሰሜን በኩል፥ በመግቢያው የቅናቱ ጣዖት ነበረ።
ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፥ ስበክ፦ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።
እኔም፦ “ጌታዬ፥ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልኩት። ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ፦ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አሳይሃለሁ” አለኝ።