ዘካርያስ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “በሰናዖር ምድር ቤት ሊሠሩለት ይወስዱታል፤ መቅደሱም በተዘጋጀ ጊዜ፥ እዚያ በስፍራው ይኖራል” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ቤት ሊሠሩለት ወደ ባቢሎን ምድር ይወስዱታል፤ በተዘጋጀም ጊዜ ወስደው በቦታው ያስቀምጡታል” አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ወደ ሰናዖር ወስደው ቤት ሊሠሩለት ነው፤ ቤቱ ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ቅርጫቱን በዚያ ያኖሩታል” አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ በሰናዖር ምድር ቤት ይሠሩለት ዘንድ ይወስዱታል፣ በተዘጋጀም ጊዜ በዚያ በስፍራው ይኖራል አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ በሰናዖር ምድር ቤት ይሠሩለት ዘንድ ይወስዱታል፥ በተዘጋጀም ጊዜ በዚያ በስፍራው ይኖራል አለኝ። |
በዚያን ቀን፤ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደገና የተረፈውን የሕዝቡን ትሩፍ ከአሦር፤ ከታችኛው ግብጽ፤ ከላይኛው ግብጽ፤ ከኢትዮጵያ፤ ከኤላም፤ ከባቢሎን፤ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።
እርሱ፦ “ለረጅም ጊዜ በምርኮ ስለምትቆዩ ቤቶችን ሠርታችሁ ተቀመጡ፥ አታክልትንም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ” ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢሎን ልኮአልና።’ ”