ትዕቢተኞቹ ግዙፋን በጠፉበት በጥንት ዘመን፥ የዓለም ተስፋ በመርከብ ተጠለለ፤ በእጅህም እየተመራ የአዲሱን ትውልድ ዘር ለመጪው ዘመን አቆየ።
ቀድሞም ትዕቢተኞች ረዓይት በጠፉ ጊዜ የዓለም ተስፋ በመርከብ ተጭኖና ተጠግቶ ዳነ፥ በእጅህም ተመርቶ የሰውን ዘርዕ ለዓለም አተረፈ።